ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ለ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ለገ/ሕ/ሥራ ማህበራት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ጨረታ ማስታወቂያ
ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ለ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ለገ/ሕ/ሥራ ማህበራት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የመወዳደሪያ መስፈረቶች የሚከተሉት ናቸው።
- ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፍቃድ ፣ ለዘመኑ የታደሰ ግብር እና ታክስ ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ቢያንስ 10 የማጓጓዥያ ተሽከርካሪዎች ስለመኖራቸው የሚያሳይ ማስረጃ እና የመጫን ችሎታቸውን ከመንግሥት አካል ለዘመኑ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ለጨረታው ቢያስን የሁለት ዓመት (የ2015 እና የ2016 ዓ.ም) የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ የስራ ልምድ ማቅርብ የሚችል፤
- ለዘመኑ የታደሰ የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ መልካም ስራ አፈጻጻም የድጋፍ ደብዳቤ ከሰሩበት አካል ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8% CPO ከኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከሲንቄ ባንክ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወድያውኑ ይመለሳል፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ስራ ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የማጓጓዣ ታሪፍን በተመለከተ አንዱን ኩንታል ከሚጫንበት መጋዘን (ታጠቅ) እስከ መሠረታዊ የሕ/ሥ/ማህበራት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 2,000.00 ባንከ በማስገባት ከዩንዬኑ በመግዛት የሚጓጓዝበትን ዋጋ በኩንታል በሁሉም ወረዳ ላይ መስጠት አለባችው ፤ ተጫራቾች በሁሉም ወረዳዎች ዋጋ የማይሰጡ ከሆነ ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መከፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ ሕጋዊ የሆነ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙት ፊት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ተከታታይ የስራ ቀን ጀምሮ በ21ኛ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡10 ሰዓት ጧት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- በተቀራራቢ ጣቢያዎች ላይ የተጋነነ የዋጋ ልዩነቶችን ለማስታረቅ ሲባል ዩኒየን የራሱን አማራጭ መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-7 ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ወይም ዶክመሜንት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቴክኒክና ፋይናንስ በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተብ ፣ ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ በትራንስፖርት ጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011-237-09-71 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሮቢ በርጋ የገበሪዎች ሕብርት ሥራ ዩኒዬን
