Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Pipe Factory (APF) (የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-35-98-37-29
  • Websitehttps://www.amharapipe.et/
  • Deadline05 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Transportation Service And Cargo

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ (Amhara Pipe Factory plc) ከቃሊቲ እና ሞጆ ደረቅ ወደቦች ጥሬ ዕቃ የያዙ ባለ20ft እና ባለ40ft ኮንቴነሮችን ወደ ባህርዳር ለማጓጓዝ እና ጥሬ ዕቃው ከተራገፈ በኋላ ባዶ ኮንቴነሮችን ወደ ደረቅ ወደቦች ተመላሽ ለማድረግ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡


የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

   የጨረታ ቁጥር APF/10/2017/Local

 

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ /የተ/የግል ኩባንያ (Amhara Pipe Factory plc) ከቃሊቲ እና ሞጆ ደረቅ ወደቦች ጥሬ ዕቃ የያዙ ባለ20ft እና ባለ40ft ኮንቴነሮችን ወደ ባህርዳር ለማጓጓዝ እና ጥሬ ዕቃው ከተራገፈ በኋላ ባዶ ኮንቴነሮችን ወደ ደረቅ ወደቦች ተመላሽ ለማድረግ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

እነርሱም :-

  1. 2017 በጀት ዓመት የታደሰ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲሁም የግብር ከፋይነት የምስከር ወረቀት (TIN) እና የመድን ሽፋን የቦሎ ምርመራ የምስክር ወረቀት ያለው ሆኖ እነዚህን ሠነዶች copy በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ከላይ በተ. 1 ላይ የተገለፀውን የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የማያቀርቡ ከሆነ በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ ተቋም 2016 በጀት ዓመት የገቢ ግብር የመፈያ ጊዜ ያሳለፉበትን ምከንያት የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረበ የሚችል መሆን አለበት፡ :
  3. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት ድረስ በፋብሪካው የፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 103 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን አንዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራች ድርጅቶች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሠነዱን መግዛት የግድ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን የገንዘብ መቀበያ ደረሠኝ ኮፒ በማድረግ ከዋጋ መሙያው ጋር አባሪ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀው ቢኖርም በአካል በመገኘት ሠነዱን መግዛት የማይችሉ ተጫራቾች በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ገንዘቡን ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን
  1. በኢ-ሜይል አድራሻችን amharapipefictory@gmail.com በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ e-mall ማግኘት ይችላሉ፡፡
  1. ተወዳዳሪ ድርጅቱ ለውድድሩ ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም ማለትም (Amhara Pipe Factory plc) በማሰራት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለዚህም ለመነሻነት ይሆን ዘንድ የሚጓጓዙ ኮንቴነሮች ብዛት 80 ባለ20ft እና 50 ባለ40ft ይሆናሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱትን የህጋዊነት ሰነዶች ቅጅ፣ የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ እና ሌሎችን ማስረጃዎች 2 ፓስታ በማሸግ እና ኮፒ እና ኦርጅናል በሚል በመፃፍ በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው 15ተኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 800 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በየኮንቲነሮች አይነት በውድድሩ በሚገኘው የአንዱ ተሽከርካሪ የደርሶ መልስ ዝቅተኛ ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡
  6. አሸናፊው የደረቅ ጭነት ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት 5 የስራ ቀናት በኋላ የጠቅላላ የማጓጓዣ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO በማቅረብ ውል የመያዝ ግዴታ አለበት
  7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29 /09-18-08-16-23 መደወል ይችላሉ፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም

 

አማራ  ፓይፕ  ፋብሪካ  /የተ/የግ/ማህበር

ባህር ዳር

Save Tender