ድርጅታችን ከለሚ ናሽናል ሲሚንቶ፤ ከሙገር ዋናው፤ ከሙገር ታጠቅ፤ ከዳንጎቴ፤ ከደርባ፤ ከኢትዮ ሲመንት እና ከሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የገዛውን ሲሚንቶ ወደ አዲስ አበባ የድርጅቱ ቅ/ፍ ማዕከላት ለማጓጓዝ ለ6 ወር በሚቆይ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፤
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/17
ድርጅታችን ከለሚ ናሽናል ሲሚንቶ፤ ከሙገር ዋናው፤ ከሙገር ታጠቅ፤ ከዳንጎቴ፤ ከደርባ፤ ከኢትዮ ሲመንት እና ከሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የገዛውን ሲሚንቶ ወደ አዲስ አበባ የድርጅቱ ቅ/ፍ ማዕከላት ለማጓጓዝ ለ6 ወር በሚቆይ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፤
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ድርጅቶች
- በጨረታ መመሪያው ላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች በሙሉ መወጣት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የብቃት ማረጋገጫ፤ ተጨማሪ አሴት ታክስና የግብር ክፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት ሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሲሚንቶ ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሽገና የተጫራች ድርጅቶች ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ (ፖስታ) አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ታኅሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ::
- ጨረታው በተመሳሳይ ታኀሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-22-50
www.eiide@eiide.com.et
