የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አለምገና ዲስትሪክት በጨረታ ቁጥር 035 የወጣውን እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አለምገና ዲስትሪክት በጨረታ ቁጥር 035 የወጣውን እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
|
የግዥ ምድብ |
|
ሎት 1 |
የሰራተኞች አልባሳት |
|
ሎት 2 |
የሰራተኞች ጫማዎች |
|
ሎት 3 |
የጽዳት እቃዎች |
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ፡-
-
- በ2017 ዓ.ም ለዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የአቅራቢነት ምዝገባ፤ እና ከገቢ ግብር ነጻ ማስረጃ ጨረታ እስከሚገባበት ቀን የሚያገለግል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት አለምገና ከሚገኘው የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡደን መሪ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 500.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ የገዙ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሰም ያልታሸገ የተጫራች ፖስታ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል። ተጫራቾች መጫረቻ ሰነድ ሲያስገቡ ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል በመጫረቻ ሰነዱ ሲያስገቡ ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል በመጫረቻ ሰነዱ በተገለፀው መልኩ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ናሙና ያላቀረቡ ውድቅ ይደረጋሉ። በመ/ቤቱ ዋጋ መሙያ ያልተሞላ ዋጋ ፊርማና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት የመስሪያ ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ በመምጣት ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጨረታው ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 በግዢ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አለምገና ዲስትሪክት
የግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ አለምገና
ስልክ ቁጥር 0113 38 13 23
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
