በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በቱሉ-አውሊያ ከተማና በሰኞ ገበያ ታዳጊ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ሞተር ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሮሎ፣ ዳምፕትራክ፣ ሻወር ትራክ፣ ሎደርና ኤክስካቫተር በጃካመር ማሽኖችን የኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ጊ/ከ/አስ/002/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በቱሉ-አውሊያ ከተማና በሰኞ ገበያ ታዳጊ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ሞተር ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሮሎ፣ ዳምፕትራክ፣ ሻወር ትራክ፣ ሎደርና ኤክስካቫተር በጃካመር ማሽኖችን የኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከክፍል ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-2-40-58-69 ወይም 09-10-34-36-29/ 09-10-63-07-77 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር
ገንዘብ ጽ/ቤት