የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን የተለያዩ ፓርኮችን ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - 36/2017
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም:-
ሎት 1፡- ተክለ ሀይማኖት ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 2፡- ልደታ መልሶ ማልማት ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 3፡- ሚሊንየም ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 4፡- ካሌብ ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 5፡- ጎላ ፓርክን ሙሉ በሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት በታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለእያንዳዳቸው ሎቶች 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንከ ጋራንቲ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ ባለው 11ኛው ቀን አስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 011-5-57-29-17/ +251-7-03-61-44-56 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
