የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት እንዲሁም የሲዲኤ ፕሮጀክት የ2015 ዓ.ም እና የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የተሰሩ የሒሣብ እና የሰው ኃይል ሥምሪት ሥራዎችን በውጪ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈልግ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋልማ/ጨ-1/1425/17
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት እንዲሁም የሲዲኤ ፕሮጀክት የ2015 ዓ.ም እና የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የተሰሩ የሒሣብ እና የሰው ኃይል ሥምሪት ሥራዎችን በውጪ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈልግ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው (ያላት)
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሥከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚገዙበት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው በወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ22ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 2 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሲል ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) ዋና መስ/ቤት
