በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ብዛት 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ፒፒሲ ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ኮምቦልቻ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 003/2017
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ብዛት 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ፒፒሲ ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ኮምቦልቻ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፤
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ ፈቃዳቸው በቂ የጭነት ትራንስፖርት አቅም ያላቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ (የመልካም የስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ) የሚችሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል በኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት መግዛትና ጨረታውን መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲስትሪከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ :- 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 551 02 05/ 033 551 22 68/ 033 551 30 02 እና 0912 84 85 80 ማግኘት ይችላሉ::
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ
መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
