በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከ2008 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን ሂሳብ መስፈርቱን የሚያሟሉ ኦዲተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2017
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከ2008 በጀት ዓመት እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን ሂሳብ መስፈርቱን የሚያሟሉ ኦዲተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም ፣
- ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል የሙያ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት እና ሌሎች አስፈላጊ ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ተቀባይነት ያላቸውን የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች መሰረት በማድረግ ኦዲት ማድረግ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተወዳዳሪዎች የድርጅታቸውን የግል ታሪክ መግለጫ /profile/ ማቅረብ የሚችሉና ቢያንስ አምስት ዓመትና በላይ የስራ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት የብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክክለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ/ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጭ (መዝጋቢ አካል) የተሰጠ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የድርጅታቸውን የግል ታሪከ መግለጫ /profile/ ለብቻ በማሸግ እና በተጨማሪም የሚሰሩበትን ዋጋ ለብቻ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማህተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስፋይ አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከረፋዱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል።
- ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ምርመራውን ኦዲት ማድረግ የሚችሉት የኢንተርፕራይዙ ዋና ጽ/ቤት በሚገኝበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ነው።
- አሸናፊ ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንከ የተመሰከረለት CPO ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ህጐች ማከበር አለበት።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 899 8018/15 መጠቀም ይችላል
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
