በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማልጋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በኩል የጉጉማ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ሊሰራ ያቀደው መሰረተ ልማት ለመንገድ ስራ የሚሆን ጠጠር የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማልጋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በኩል የጉጉማ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ሊሰራ ያቀደው መሰረተ ልማት ለመንገድ ስራ የሚሆን ጠጠር የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ያላቸውና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በግንባታ አፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ተጫራች ጨረታውን መወዳደር አይችልም፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለ21 /ሀያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን 1 ኦሪጅናልና 1 ፎቶ ኮፒ የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና በፖስታ ለየብቻቸው በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በማልጋ ወረዳ ግዥ/ፋይ/አስ/ር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ይህ ጨረታ በ22ኛው ቀን 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው አለመገኘታቸው ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የጨረታ ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% CPO /Bid bond/ bid security/ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- አሰሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማልጋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ ጽ/ቤት
