ፀሀይ ባንክ አ.ማ Technical Support (Hardware & Software) and License Renewal On Cisco, Fortinet and F5 BIG-IP Solutions ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0009/2017
ፀሀይ ባንክ አ.ማ Technical Support (Hardware & Software) and License Renewal On Cisco, Fortinet and F5 BIG-IP Solutions ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን::
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርተፍኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸዉ ይገባል::
- ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወለል ላይ በመክፈል 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 7ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም::
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አዲስ አበባ ለገሃር ስልክ ቁጥር
0115583187/0115581699
ፀደይ ባንክ አ.ማ
