የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ሎት 1) የኖራ ውህድ ሎት 2) የአልጋ ፍራሽ ሎት 3) የኖራ ማጓጓዥያ ትራንስፖርት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ሎት 1) የኖራ ውህድ ሎት 2) የአልጋ ፍራሽ ሎት 3) የኖራ ማጓጓዥያ ትራንስፖርት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለ2017 በጀት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- ለአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማቅረብ የምትችሉ ሆነው በጨረታ መክፈቻ ዕለት ኦርጅናል የህጋዊነት ሰነዳቸውን ለማመሳከሪያነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከi-5 የተጠቀሱትን የህጋዊነት ሰነዶች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአልጋ ፍራሽ በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ያለተጨማሪ ወጭ እስከ ዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (BID Security) 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ፣ (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (Unconditional BID BOND) ማስያዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ 15ተኛው (አስራ አምስተኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክን አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመሙላት ፣ የህጋዊነት ሰነዶችን ፎቶግራፊከ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (BID Security) በማዘጋጀት እና በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ እላዩ ላይ ማህተም ፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታታይ 16ተኛ (አስራ ስድስተኛው) ቀን 4፡00 ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ተኛ (አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ: መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-881-3338 ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መደወል ይቻላል፡፡
ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አርባ ምንጭ
