Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Media Network (AMN) (የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ)
  • Address 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ። ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1116382
  • Websitehttps://www.amn.gov.et/ Website
  • Deadline08 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Electrical And Electromechanical

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የእቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ......008/2017

 

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 2017 በጀት ዓመት የእቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት

ሎት 1 የሬዲዮ ስቱዲዮ መሳሪያዎች ግዥ በድጋሚ የወጣ

ሎት 2 55 inch television ግዥ በድጋሚ የወጣ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ያላቸው፤ የዘመኑን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የነቢዎች ክሊራንስ ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቶች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፈርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 1 ጨረታ 20 የስራ ቀናት ለሎት 2 ጨረታ 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 28 በመገኘት የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ለሎት 1 እና ለሎት 2 ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ
  6. የሎት 1 ጨረታ የሚከፈተው 21ኛው ቀን ሲሆን የሎት 2 ጨረታው የሚከፈተው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን / ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  9.  በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ 15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
  10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡-

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም /ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ። 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011 1 11 63 82 መደወል ይችላሉ፡፡

 

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

 

 

Save Tender