Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Media Network (AMN) (የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ)
  • Address 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ። ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1116382
  • Websitehttps://www.amn.gov.et/ Website
  • Deadline16 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Electrical And Electromechanical

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸውን እቃዎች ፤ ሎት 1. ኤልኢዲ ስክሪን እና ተዛማጅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ግዥ፣ እና ሎት 2. በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.ብ.ግ.ጨ.009/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 2017 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸውን እቃዎች፤

ሎት 1. ኤልኢዲ ስክሪን እና ተዛማጅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ግዥ፣

ሎት 2. የደንብ ልብስ ግዥ በድጋሚ የወጣ፣

በጨረታ ቁጥር ......009/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፤-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው::
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ላሉት ጨረታዎች 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 28 የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው 11ኛው ቀን ከቀኑ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 430 ሰዓት ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  9. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ 15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
  10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም

/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ፡- 011 111 63 82 መደወል ይችላሉ፡

 

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

 

Save Tender