ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 03/2017
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃላ/የተ/የግ/ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ያገለገሉ መካኒካል ማሽንስና ስፔር፣
- ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ሞተሮች፣
- የብረት በርሜል፣
- ያገለገሉ ብላደሮች፣
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣
- የፈርነስ ፍሳሽ፣ ያገለገለ ዘይት፣
- የተቆራረጡ ብረታ ብረቶች፣
- የተቆረጡ ጎማዎች፣
በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት በ4፡05 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ፡- ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥር ፡- 011-4-42-15-55/234 ወይም 09-43-88-03-72 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ
