የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለአንደኛና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመማሪያ ማስተማሪያ እቃዎች እና ፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ማወዳደር ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለአንደኛና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመማሪያ ማስተማሪያ እቃዎች እና ፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ማወዳደር ይፈልጋል። ስለሆነም -
- በጨረታው መወዳደር የሚችሉ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ያላቸው፤
- በተመሳሳይ ተግባራት አገልግሎት በመሳተፍ ልምድና መልካም የስራ አፈፃፀም ተገቢውን ካፒታልና ውስጣዊ ብቃት ያላቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቢሮ ቁጥር 05 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሠዓት ይከፈታል፣
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 0336660125/26
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ትምህርት ቢሮ
ሰመራ
