ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ለሥራ የሚፈልጋቸውን ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችንና የቪድዮ ካሜራ አክሰሰሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ለሥራ የሚፈልጋቸውን ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችንና የቪድዮ ካሜራ አክሰሰሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዚህ ጨረታ መወዳደር የሚችሉ ፡-
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍከት ያላቸው
የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፊከት ያላቸው ድርጅቶች ሀዋሳ ሲዳማ ቡና ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 እየከፈላችሁ እንድትመዘገቡና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO እንድታቀርቡና የጨረታውን የመወዳደሪያ ዋጋ ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ ሥራ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 03 በሚገኘው ጨረታ ሳጥን እንድታስገቡና ጨረታውም በ8ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916037261 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
