በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ፡-
- የትምህርትና ስልጠና ዕቃዎች ግዥ
- የቢሮ የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ
- የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- የተሽከርካሪዎች ግዥ እና
- የደንብ ልብስ ግዥ ሲሆን
ሁሉም የተጠቀሱት ዕቃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ስለሆንም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ቲን ነምበር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግዥና ንብ/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 15 በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ብር 5.000 (አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃዎች ናሙና/ሳንፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች (ድርጅቶች) ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ መሸነፋቸው ከተረጋገጠ ጀምሮ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃዎች ቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ቀጥሎ ባለው በስራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር :- 046 465 06 72/09 10473134/09 12406268
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ት/ትና ስልጠና ቢሮ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
