በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ለወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለሚዲያ ሥራ አገልግሎት የሚውል የኤሌትሮኒክስ ዓይነቶች በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ለወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለሚዲያ ሥራ አገልግሎት የሚውል የኤሌትሮኒክስ ዓይነቶች በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ዲጂታል ካሜራ ግዥ
- ሞንታሪቦ /ማስተር ሳውንድ/ ግዥ ስለሆነም በመንግሥት ግዢ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት:-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በዘመኑ ግብር የተከፈለበት፣
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር / Tin Number/፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ከውል ዋጋ ላይ 2% የመንግስት ግብር ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
- EGP ኦላይን ምዝገባ መረጃ በሀርድ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ጨረታውን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ አሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ሆኖ ስማቸውን፣ ፊርማቸዉን አድራሻቸዉንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነትን በትክክል ማስፈርና በማሸግ በቁ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ላይ ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላዉ ዋጋ ላይ የዉል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፣
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሥራ ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ሥራ ቀናት በቁጫ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረዉ መሰረት ጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ28 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛዉ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል አለመገኘት የጨረታውን መክፈትን እያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታ ሂደት አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት ያሸነፉበት ዕቃዉን ወደ ቁጫ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ጫኝ አወራጅን ጨምሮ ማድረስ አለበት ።
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ ጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0464590393 ደውሎ ይጠይቁ።
ስልክ ቁጥር ፡- 0917170976/0916138074
የቁጫ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
