የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት በፍ/ባለመብት እነ አቶ አጂቦ መሀመድ /6 ሰዎች/ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 94431 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 ላይ ያለ 3 ቤቶች የሆነ ቤት እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ አጂቦ መሀመድ /6 ሰዎች/ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 94431 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 የቤት ቁጥሩ 1690፣ የካርታ ቁጥር 3862 የሆነ በ178 ካ/ሜ ላይ ያረፉ 3 ቤቶች የሆነ ቤት እና ቦታ መነሻ ግምቱ ብር 848,436.62 /ስምንት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር 62/100/ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ቤቱን እንዲጎበኙ የሀራጅ ሽያጩ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡
ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡50 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ይከናወናል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የሃራጅ ጨረታው ከመመዝገቡ በፊት የዚህን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዞ እንዲመዘገብ በCPO ያልያስያዘ የማይመዘገብ ሆኖ የሃራጅ ሽያጭ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ አጠቃሎ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ እንዲያደርግ፡፡
ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የድሬዳዋ ምድብ
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት
