Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Center for Development /ECD/ /ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት/
  • Address ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0982-882826
  • Websitehttps://ecdethiopia.org/
  • Deadline21 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Printing And Publishing

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ ስድስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ጋር በመሆን ለሚተገብረው "Mobile toolkit for Climate Resilience (MICR)" ፕሮጀክት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የትምህርት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የሚጠቅሙ የተለያዩ ህትመቶችን ለማሳተም ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ገኙ ስድስት ንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ጋር በመሆን ለሚተገብረው "Mobile toolkit for Climate Resilience (MICR)" ፕሮጀክት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የትምህርት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የሚጠቅሙ የተለያዩ ህትመቶችን ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን የህትመት ውጤቶች መሥራት የምትፈልጉ በዘርፉ የተሰማራችሁ የህትመት ተቋማት በውድድሩ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. የፍላየር ህትመት
  2. የፖስተር ህትመት
  3. የፍላሽ ካርድ (ለአየር ንብረት ለውጥ ትምህርት የመርጃ መሣሪያ የሚሆን)
  4. የባነር ህትመት ከነ ቋሚ ብረቱ (እግር)

ሲሆኑ በዘርፉ የተሰማራችሁ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  3. ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  4. የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  5. ህትመቶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት በጥራት ማተም የሚችሉ እና ባነሩ ከነ ቋሚው ተዘጋጅቶ ለመተከል ዝግጁ ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ህትመቶቹን በራሳቸው ትራንሰፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ቦታ ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣ አስፈላጊውን የመንግስት ግዴታዎች ያሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ በነፃ በመውሰድ ህትመቶቹን የምታትሙበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ አድርጋችሁ እንድትወዳደሩ እንገልፃለን፡፡

 

አድራሻ - ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቨሎፕመንት /ECD/

ህንፃ 7 ፎቅ

ስልክ :- 011 663 95 16/17

አዲስ አበባ

 

ማስታወሻ ፡- ድርጅታችን ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቬሎፕመንት /ECD/

 

Save Tender