Tender Detail

Tender Details

  • Company Lideta Manufacturing College (የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ)
  • Address ኢስት አፍሪካ ቦትሊግ አክሲዮን ማህበር ኮካ ኮሳ ፋብሪካ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112736494
  • Website
  • Deadline27 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት እቅድ ማስፈፀሚያ የሚሆኑ የስልጠና ግብዓቶችን እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን የቀረበውን ፍላጎት በ15 የተለያዩ ሎቶች በመለየት የሚከተለውን መስፈርት ከሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 2017 በጀት አመት እቅድ ማስፈፀሚያ የሚሆኑ የስልጠና ግብዓቶችን እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን የቀረበውን ፍላጎት 15 የተለያዩ ሎቶች በመለየት የሚከተለውን መስፈርት ከሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች 2 ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ-

  1. ከላይ ያሉትን እቃዎች መሰረት በማድረግ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች።
  2. ለሚጫረቱበት ሎት (ዘርፍ) ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (ቲን ነም) የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ በአንድ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ሂሳብ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በኮሌጁ የግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. የጨረታው ሰነዱ መቆያ ጊዜው 60 ቀናት ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ የሰነድ ምገማው ካላለቀ በመንግስት ግዥ መመሪያ ቁጥር 3/2022 መሰረት እስከ 28 ቀናት ሊጨምር ይችላል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ኮሌጁ ባስቀመጠው ዝርዝር መሰረት ዋጋቸውን በመሙላት እና ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት በግልጽ በመጻፍ ለየብቻ አሽገው እና ሁለቱንም ሽጎች በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የደንብ ልብስ፣ የፅዳት የፅህፈት የፈርኒቸር እና የአይሲቲ እቃዎች ላይ የተወዳደሩ ተጫራቾች ከእያንዳንዱ ዝርዝር ጋር (ከተወዳደሩበት) ሳምፕል እንዲሁም ቴክኒክ ዶክሜንት የሚቀርበው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቅድሚያ በኮሌጁ ሳምፕል ክፍል ገቢማድረግ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ቀድሞ ያልገባ ሳምፕል እና የቴክኒክ ሜንት ለውድድር አይቀርብም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለጸው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከአሪጅናል ጨረታ ስነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:-
  1. አይሲቲ (ሎት-11) 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  2. ፈርኒቸር (ሎት-7) 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  3. ጋርመንት (ሎት-10) 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  4. ብረታ ብረት (ሎት-6) 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ሲሆኑ ሌሎቹ ሎቶች በአንድ ሎት 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ አለበት፡፡
  1. አሸናፊ ተጫራቾች የአሽናፊ ደብዳቤ ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የቅሬታ ማቅረቢያ ቀናትን ሳይጨምር ያሸነፉበትን እቃ ወይም አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10 (አስር) ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝና ከእያዳንዱ እቃ አንድ ሳምፕል እና ኒክ ዶክመንት በማስገባት ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ያሸነፋቸውን እቃዎችን በሳምፕሉ መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ 11ኛው የስራ ቀናት 4:00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ (በአመች ቦታ) ይከፈታል። የጨረታ ፈቻ ቀኑ በስራ ቀን ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  4. ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ከቀረቡት ዝርዝሮች ውስጥ 20 ፐርሰንት ብዛት ለመጨመር (ለመቀነስ) መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ - ኢስት አፍሪካ ቦትሊግ ሲዮን ማህበር ኮካኮላ ፋብሪካ አጠገብ፤

ስ.ቁ :- 011-2-73-64-94

 

ደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ

 

Save Tender