በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 133.04 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ካፌ ማእከሉ አሁን ከሚሰጠው የሬስቶራንት አገልግሎት በተለየ መልኩ ለስፖርት ባርና ሬስቶራንት መስራት ለሚፈልግ ተጫራች በጨረታ አወዳድሮ ለ3 አመት ማከራየት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 133.04 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ካፌ ማእከሉ አሁን ከሚሰጠው የሬስቶራንት አገልግሎት በተለየ መልኩ ለስፖርት ባርና ሬስቶራንት መስራት ለሚፈልግ ተጫራች በጨረታ አወዳድሮ ለ3 አመት ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራች በጨረታው በማወዳደር ወደ ስራ ማስገባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸውን የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርባቸው የጫረቻ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በአስረኛው የስራ ቀን 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ከተባለው ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡ - አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትልቁ አደባባይ ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተግራ ገባ ብሎ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ
ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
