የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ በየሎቱ እንደተቀመጠው የግዥ ፍላጎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ 20/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ በየሎቱ እንደተቀመጠው የግዥ ፍላጎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ሠንጠረዥ 1
ግዥ የሚፈፀምበት የግዥ ፍላጎት አይነቶች፡-
|
ተ.ቁ |
ግዥ የሚፈፀምበት ፍላጎት አይነቶች |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ መጠን |
|
1 |
በዋናው ፖስታ ቤት የፓርኪንግ ቦታ ኪራይ |
20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር |
ስለሆነም፡-
በዚህ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ተጫራቾች የማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በማቅረብ በድርጅቱ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል እየቀረቡ የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ (በተናጠል) በጨረታ ሠነዱ ላይ በዝርዝር በተገለጸው መሠረት ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎኘ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በቅድሚያ የፓርኪንግ ቦታ ኪራይ ሲ.ፒ.ኦ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር እና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ የሚቀርብባቸው ይሆናል፡፡
የጨረታው ኤንቬሎፕ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ይከፈታል፡፡
- CPO (ሲፒኦ ) ሲያሠሩ ፡- የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ወይም ETHIOPIAN POSTAL SERVIC ENTERPRISE መሆን አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911954537 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት
