የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በ2017 ዓ.ም የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ እና ለቡናና ደን ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ፖለቲን ቲዩብ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በ2017 ዓ.ም የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
- ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ እና
- ለቡናና ደን ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውል ፖለቲን ቲዩብ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያለው፡፡
- ለአቅራቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 20,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን 1 ኦርጅናል ፋይናሻልና የቴክኒካል በ2 ኮፒ በአንድ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት 8፡00 ሰዓት የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ባለስልጣን ግዥ ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ግዥ ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት፡፡
በስልክ ቁጥር፡- 0462122897 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
