የመብራት መቆጣጠርያ ዕቃ /AVE (Automatic Votage Regulator) WTH accessories የቤኒሻንጉልጉሙዝ ሚዲያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017
የመብራት መቆጣጠርያ ዕቃ /AVE (Automatic Votage Regulator) WTH accessories የቤኒሻንጉልጉሙዝ ሚዲያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የመብራት መቆጣጠሪያ ዕቃ /AVE (Automatic Voltage Regulator) WITH accessories ዕቃ ግዥ በዚህ መሰረት በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገበበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ቲን ነምበር ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጳውሎስ ሆስፒታል ቢታንያ ክሊኒክ ገባ ብሎ በመሄድ በ100 ብር ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ቢድ ቦንድ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በቤኒሻንጉል ጉመዝ ሚዲያ ስም ሞልተው ከኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2 /ሁለት/ ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2/ ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በትክክል መቅረብ አለበት የኮፒ ሰነዶች በአይነትም ሆነ በብዛት ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታውን በ16ኛው ቀን እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን ሞልተው አዲስ አበባ በሚገኘው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጳውሎስ ሆስፒታል ቢታንያ ክሊኒክ ገባ ብሎ በሚዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው ::
- ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0910000329፣0928653853፤ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ
