Tender Detail

Tender Details

  • Company አባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንፃ በሚገኘው ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም ባሕር ዳር ንጋት ኮርፖሬት ዋናው መ/ቤት ቀበሌ 16 አምባሰል ሕንፃ ጀርባ ንጋት ኮርፖሬት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 03 ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912028400
  • Website
  • Deadline26 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-26 00:00:00
  • Categories Stock Sale

የአባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ባለአክሲዮኖች በኩባንያው ውስጥ ያላቸውን አክሲዮን በዚህ የጨረታ ሰነድ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልቶ አክሲዮን ለሚገዛ ማንኛውም ተጫራች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የአባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

የባለአክሲዮኖች የአክሲዮን እጣ ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ


 

የአባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ባለአክሲዮኖች በኩባንያው ውስጥ ያላቸውን አክሲዮን በዚህ የጨረታ ሰነድ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልቶ አክሲዮን ለሚገዛ ማንኛውም ተጫራች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

  1. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚከናወነው በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንፃ በሚገኘው ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም ባሕር ዳር ንጋት ኮርፖሬት ዋናው መ/ቤት ቀበሌ 16 አምባሰል ሕንፃ ጀርባ ንጋት ኮርፖሬት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 03 ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት/ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

  2. የማኅበሩን ባለእከሲዮኖች አክሲዮን ለመግዛት ፋብሪካውን ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የአባይጥጥ ማዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በአማራ ከልል፤ አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፤ በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከተማ በ02 ቀበሌ ይገኛል፡፡ 

  3. ኩባንያው በዋናነት መሠረታዊ የሚባሉ መሠረተ ልማቶች (መንገድ፣ መብራት፣ ውሃ እና ስልክ) የተሟሉለት ሲሆን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 20 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ በኩባንያው ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን አክሲዮን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ጨረታው በጋዜጣ (በማስታወቂያ) ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31 ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በአዲስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንጻ በሚገኘው ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

  5. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይሲሆን 31ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ በሚገኘው ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።

  6. ተጫራቾች የአክሲዮኖችን ዕጣ ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የሚሆን ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባለአክሲዮኖች በአንዱ ማለትም በንጋት ኮርፖሬት ስም በማሠራት ኦርጂናሉን ከጨረታ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ከሞሉት ዋጋ ጋር ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::

  7. ባለአክሲዮኖች በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙበታቸው የተጠበቀ ነው፡፡

  8. ባለአክሲዮን ማለት በኩባንያው ውስጥ የአክሲዮን ባለቤት የሆኑትን ንጋት የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት ፣ አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እና ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት ድርጅት ማለት ነው፡፡

  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0912028400 ወይም 0933634958 ወይም 0912960687 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡



አባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

Save Tender

የአባይ ጥጥ መዳመጫ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ባለአክሲዮኖች በኩባንያው ውስጥ ያላቸውን አክሲዮን በዚህ የጨረታ ሰነድ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልቶ አክሲዮን ለሚ...

READ MORE