Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-681-32-41
  • Website
  • Deadline12 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-12 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በብሔራዊ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በብሔራዊ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል። ውድድሩም በጥቅል ድምር ዋጋ ነው :

ስለሆነም :-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው

  3. የግዥው መጠን ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው መቅረብ አለባቸው::

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

  7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

  8. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡

  9. ጨረታው 16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 400 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ይከፈታል። ሆኖም የጨረታ መከፈቻው ዕለት የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው በተመሣሣይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

  10. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ በሌላኛው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የለበትም ፡፡

  11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ቢሮ ቁጥር 22 በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 681-32-41 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

  12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::


 

የሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

/ብርሃን

Save Tender