Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ሀላባ ቁሊቶ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline16 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-16 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-6ኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።


 

 የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-6ኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ይሆናል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን በብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።

2. ጨረታው በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ግን በመክፈቻው ቀን የተጫራቾች ያለመገኘት መምሪያው ጨረታውን ከመከፈት የሚያስተጓጉለው ነገር አይኖርም።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ ዋስትና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።

4. የጨረታው አሸናፊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ወይንም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

6. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

በማዕ/ት/ክ/መ/ የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

  

Save Tender