የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአስፓልት ዓይነቶችን ከአዲስ አበባ-ድሬዳዋ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአስፓልት ዓይነቶችን ከአዲስ አበባ-ድሬዳዋ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
-
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በመንግሥት ግዥና አገልግሎት በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታው የሚሳተፉት በወኪል አማካኝነት ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ እና ሕጋዊ የወኪል መታወቂያ ኮፒዎችን አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል
-
አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አስፈላጊውን ሁሉ አሟልተው ንብረቱን በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማጓጓዝ ግዴታ አለባቸው
-
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይዘጋል በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል
-
የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር 025 111-13-13 /09 27 63 61 26/ 09 19 00 80 17
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
