Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115572949
  • Websitehttps://aacaprac.gov.et/?lang=ahm
  • Deadline13 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-13 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየትና እና ለመግዛት ይፈልጋል። 


 

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 66/2017

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን

  • ሎት 1፡- የፈረንሳይ ፓርክ፣ ኮልፌ ፓርክ፣ አቃቂ ፓርክ፣ ከንቲባ ቢትወደድ ፓርክ በውስጡ የሚገኙ አዳራሾችን ፣ሱቆችንና ካፍቴሪዎችን ለማከራየት፣

  • ሎት 2፡- ገዳመ ኢየሱስ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት

  • ሎት 3፡- ለጽዳት እቃዎችን ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየትና እና ለመግዛት ይፈልጋል። 

በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው።

  2. ተጫራቾች ለውሃ ቦቴ ትራንስፖርት አገልግሎት 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር) ሲሆን ለሌሎቹ ሎቶች ደግሞ 20,000 (ሀያ ሺ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ ባለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

  6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

  7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 011 557 2917/ 251 70 361 4456 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን

  

Save Tender