Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address , Phone: 046-212 1580
  • Website
  • Deadline23 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-23 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2013 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን በድርጅቱ የተንቀሳቀሰውን ንብረት በውጭ የሂሳብ አዋቂዎች የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት የማቅረብ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

በድጋሚ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት ማቅረብ አገልግሎት

የግዥ መለያ ቁጥር የእሥ/06/2017

 

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2013 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን በድርጅቱ የተንቀሳቀሰውን ንብረት በውጭ የሂሳብ አዋቂዎች የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት የማቅረብ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት የአገልግሎት ዘርፎች የታደሰ የንግድ ፍቃድና የውጭ የሂሳብ አዋቂዎች ማሟላት ያለባቸው

1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሙያ ፈቃድ የተሰጠው እና የ2016 ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ፍቃድ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ዋና ቢሮ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የግዢ ብድን መሪ ቢሮ ከድርጅቱ ዋና ቢሮ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስም ተዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ውጪ የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ሳይከፈት ውድቅ ይሆናል።

5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ስማቸው ሙሉ አድራሻቸው ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ብድን መሪ በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላል።

7. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አደራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የድርጅቱ አድራሻ፡

ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ወይም ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው አስፓልት መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ከአዜብ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል አጠገብ።

የስልክ ቁጥር 046-212–9112/ 046-2212-1580

ፓ.ሳ. ቁ. 190

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ

አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender