Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibir Construction Corporation (ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባህር ዳር ከተማ አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ዋና መ/ቤት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-320-35-76
  • Websitehttps://arwe.et/
  • Deadline18 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-18 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

ኮርፓሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ለተገለፁትን የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርቱን አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል።


 

የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ኀኮኮ14/2017

 

ኮርፓሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ለተገለፁትን የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ የተሰማሩ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርቱን አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል።

 

.

ሲሚንቶው የሚጫንበት ቦታ

መለኪያ

የሚጫነው ሲሚንቶ ብዛት

ፒፒሲ ሲሚንቶው የሚራገፍበት ቦታ

1

 

 

ለሚ (ኢስት አፍሪካ ናሽናል ዲስትሪቢውሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ)

 

 

በኩንታል

 

 

 

4,500

ደሴ

7,500

ወራቤ ቦጆ በር አስፓልት ፕሮጀክት

12,000

ባህር ዳር ከተማ

3,000

ወልዲያ ከተማ

3,000

ደንበጫ ፈረስ-ቤት አስፓልት ፕሮጀክት

 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ..ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ቁጥር እና ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ክሊራንስ ሰርትፍኬት እና 10 /አስር/ እና ከዚያ በላይ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪ ያላቸው እና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀን የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
  3. ኮርፓሬሽኑ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የጭነቱ መጠን እንደአስፈላጊነቱ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የዋጋ መሙያ ላይ የንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርፍኬት እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያቸውን ዋጋ መሙያዉ ዋና ላይ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕርዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና /ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፓሬሽን አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው 15ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በዚሁ ቀን 4:30 ይከፈታል። ይሁን እንጂ 15ኛው የመክፈቻ ቀን ከኮርፓሬሽናችን የስራ ሰዓት ውጭ ከሆነ እና የመንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  6. በጨረታው ለተገለፀወ የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከኮርፓሬሽኑ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  7. ኮርፓሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ።

 

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

 

Save Tender