በአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረብርሀን ግብርና ምርምር ማዕከል በ/ሰ/ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ ፋጂ /ኤልካ አካባቢ የሚገኘውን የለማ የማዕከሉን ደን በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረብርሀን ግብርና ምርምር ማዕከል በ/ሰ/ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ ፋጂ /ኤልካ አካባቢ የሚገኘውን የለማ የማዕከሉን ደን በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ስለሆነም፡-
- ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ማየት ይቻላል።
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ ከፍሎ በሥራ ቀናት መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የደን አይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ በማዕከሉ ባንክ አካውንት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከስማቸውና ከአድራሻቸው ጋር ኦሪጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደ/ብርሀን ግብርና ምርምር ማዕከል ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተፃፈ በኋላ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 21ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣው ከወጣበት ዕለት አንስቶ ላሉት 20 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በአጣና ወይም በጣውላ ንግድ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-673-69-18-ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል
