በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት በ03 ቀበሌ ጀባ የለማ የባህር ዛፍ የማህበረሰብ ደን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፊልጋል፡፡
የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት በ03 ቀበሌ ጀባ የለማ የባህር ዛፍ የማህበረሰብ ደን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፊልጋል፡፡
-
-
-
- ለጨረታው የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ማየት ይችላል።
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣውን መ/ቤት በመገኘት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በስራ ቀናት ወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን አይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዢያ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ለእያንዳንዱ ኮምፓርትመንት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉት የእያንዳንዱን ኮምፓርትመንት እና የሚገዙበትን ዋጋ ከስማቸውና ከአድራሻቸው ጋር በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎኘ በማሸግ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት የማህበረሰብ ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተፃፈበት በኋላ ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 21ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 21ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ይዘጋል፤ በእዚያው ዕለት በ21ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በአላት ቀን ከሆነ ስራው በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ይፈፀማል፡፡
- የጨረታው ተወዳዳሪ የፈለገውን ኮምፓርትመንት አንድና ከእዚያ በላይ ወይም ሁለቱንም ኮምፓርትመንቶች ዋጋ መሙላት ይችላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0901465288 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
-
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የአካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት
