ድርጅታችን ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ እና የተሰባበሩ መጠጥ መያዣ ፔት ቦትሎች እና ከዳኖቹ ፤ የፕላስቲክ ሳጥኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02
የተበላሹ የመጠጥ መያዣ ፕላስቲኮችና ክዳኖች፣ ሳጥኖች፣ ሽያጭ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ እና የተሰባበሩ መጠጥ መያዣ ፔት ቦትሎች እና ከዳኖቹ ፤ የፕላስቲክ ሳጥኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ዝርዝራቸውና ብዛታቸውን ከተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ታክስን ጨምሮ በጅምላ ዋጋ በመስጠት መጫረት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን ማንኛውም ተጫራቾች ንብረቶቹን በሰበታ ቅርንጫፍ ፋብሪካ በመገኘትና በማየት ከሚያዝያ 6 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀን ከሰኞ እስከ አርብ እስከ 10፡30 በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም በማውረድና በመጫረት መሳተፍ፤ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ መክተትና መጫረት የሚችል መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅቱ ይከፈታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0911-46-02-79 ወይም 0911-14-85-21
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
