ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለምስራቅ ጎጃም ከፍ/ፍር/ቤት ፣ ለምዕ/ጎጃም አስተዳደር ዘርፍ እና ለምዕ ጎጃም ኢኮኖሚ ዘርፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 19/2017
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለምስራቅ ጎጃም ከፍ/ፍር/ቤት ፣ ለምዕ/ጎጃም አስተዳደር ዘርፍ እና ለምዕ ጎጃም ኢኮኖሚ ዘርፍ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ያለው/ያላት፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ድረስ ብቻ ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ከዚህ በፊት ሊፍቶች /አሳንሰሮች/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ በብቃት እና በጥራት ለመስራታቸው የሚያረጋግጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማያያዝ ግዴታ መሆኑን መታወቅ አለበት።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር
ባህር ዳር- 058-218-0538/09-13-27-60-57/09-18-71-66-16
አዲስ አበባ ፡- ስልከ ቁጥር 0111265338/0930352410/0967994210
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
