Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa University (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address 6ኪሎ ዋናው ግቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-22-00-01
  • Websitehttps://www.aau.edu.et/
  • Deadline25 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-25 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቡነ-ጴጥሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የጋዜጠኝነትና ብዙሀን መገናኛ ህንጻ እና በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለወርቅ ቤት ለባንክ አገልግሎት እና ለሌሎች አገልግሎቶች የተለያዩ ቦታዎችን ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


 

የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- አአዩ/ብግጨ/የሱቅ ኪራይ/06/2016/24

 

  1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቡነ-ጴጥሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የጋዜጠኝነትና ብዙሀን መገናኛ ህንጻ እና በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለወርቅ ቤት ለባንክ አገልግሎት እና ለሌሎች አገልግሎቶች የተለያዩ ቦታዎችን ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 . እስከ 400 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማስረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ሚያዝያ 17 ቀን 2017 . 430 ሰአት ይከፈታል።
  3. ከጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት፡፡
  4. አንድ ድርጅት መጫረት የሚችለው ለአንድ ክፍል ብቻ ነው፡፡
  5. በጨረታው ቅድሚያ ክፍያ ለስድስት (6) ወር እና ከዚያ በላይ ቅድሚያ ክፍያ ለሚሰጡ ድርጅቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው፡፡
  7. በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
  8. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
  9. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  10.  ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል፡፡
  11.  ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በአገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎትን አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡
  12.  ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 312

 

ስልክ ቁጥር፡-+251 11 124 9030

 

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender