የኤስካቫተር ኬት ማሽን፣ የገልባጭ መኪና የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ቁ/ማሽ/ኪራ/0002/2017 የዲላ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደር ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በከተማ ውስጥ ለሚሠራው የልማት ሥራ የሚውል የኤስካቫተር ኬት ማሽንና የገልባጭ መኪና የኪራይ አገልግሎት ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኤስካቫተር ኬት ማሽን፣ የገልባጭ መኪና የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ቁ/ማሽ/ኪራ/0002/2017 የዲላ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደር ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በከተማ ውስጥ ለሚሠራው የልማት ሥራ የሚውል የኤስካቫተር ኬት ማሽንና የገልባጭ መኪና የኪራይ አገልግሎት ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የቀረበውን መሥፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የማሽነሪ ኪራይ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው፤
- የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው::
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የኦፕሬተር ወጪ እና የነዳጅ፣ የቅባት፣ የጥገና ወጪ መሸፈን የሚችል ሆኖ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ለእያንዳንዱ የ100,000 /የአንድ መቶ ሺህ ብር/ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማሽነሪዎችን በከተማ ውስጥ አሠሪ መ/ቤት ወደሚፈልግበት ቦታ በሎበድ ማመላለስ ጨምሮ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል 1 ኦርጅናል 2 ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 2 ፋይናንሻል ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻ ሁሉንም በአንድ እናት ኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ አድራሻቸውን በመሙላት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት
