የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ለነባሩ ህንፃ በአንደኛ መሰል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ፈርኒቸሮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ደረጃቸውን የጠበቁ ፈርኒቸሮችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/005/2017
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ለነባሩ ህንፃ በአንደኛ መሰል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ፈርኒቸሮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ደረጃቸውን የጠበቁ ፈርኒቸሮችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገው ዋናውን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው። ተጫራቾች በሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ የተደራጁ ሕጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል፣ ሁኔታዎች የሚወዳደሩበትን ተቋም ስም፣ የሚወዳደሩበትን የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ ዓይነት፣ የጨረታ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያውን የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስከር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ለመፈፀም ቃል ሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድረጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው::
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
