Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
  • Address በካፋ ዞን ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0917916439
  • Website
  • Deadline08 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-05-10 00:00:00
  • Categories Educational And Training Equipment And Machinery

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም በጀት ዘመን ለተሽከርካሪዎች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደ///// መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2017 / በጀት ዘመን ለተሽከርካሪዎች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡ ተወዳዳሪዎች

1 በሙያ መስክ ወይም በዘርፉ የተመዘገቡና ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ህጋዊ ዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ስለመሆናቸው እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባችው::

25 የዕቃው ዝርዝር መግለጫ /specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 1 ቀን ጀምሮ 14 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ባለው ፖሊ ቴክኒክ /ቤት አካባቢ እና ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥግብ/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ በኮሌጁ የሂሳብ ቁጥር 1000029122877 ላይ የማይመለስ 200 ብር በማስገባት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ትላላችሁ ፡፡

3 የምጫረቱባቸውን እቃዎች በመለየት በአይነታቸው እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ ለየብቻ ዋናና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቶችን ስም ወይም ድርጅት በመፃፍና ማህተም በመምታት የጨረታ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 1 ቀን ጀምሮ 14 /አስራ አራት/ ተከታታይ ቀናት ወይም ጨረታ የሚታሸግበት ቀንና ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4ኛ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ቢድ ቦንድ እና ቼክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

5ኛ አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

6 አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ ቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውን ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብና ማስረከብ አለባችው፡፡ ለማያቀርቡ ለውል ማስከበርያ ያስያዙት CPO አይመለስም፡፡

7የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 15ኛው ቀን ከቀኑ 9:30 እስከ 10:00 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡ 8ኛ ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት እለት ጀምሮ 30 ቀናት ይሆናል፡፡

9 የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ግዥ ንብ /አስ/ ቢሮ ቁጥር 01 ጋዜጣ ከወጣበት ልክ 17ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በጨረታ መክፈቻ ወቅት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አይከለክልም፡፡ እለቱ የእረፍት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ወደ የሚቀጥለው ስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

10 በጨረታ ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ውጭ መፃፍ አይፈቀድም።

11 ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃ የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ ከአታችሜንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ወይም የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ የማይጠቀሙ ከሆነ የማይጠቀሙበት ምክኒያት ከገቢዎች /ቤት ደብዳቤ በማስደገፍ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡

12 ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917916439/091346623/ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የደ///// መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

Save Tender