Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115572949
  • Websitehttps://aacaprac.gov.et/?lang=ahm
  • Deadline05 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-05-05 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች የፈረንሳይ ፓርክን የችግኝ ጣቢያውን ሳይጨምር ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 70/2017

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም

  • ሎት1 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽን በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪደር ልማት የለሙ በካሳንችስ ፣ ሳር ቤት ፣ ለቡ ጀሞ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ 4 ኪሎ 5 ኪሎ 24 ቀበሌ አካባቢ 22 አካባቢ መገናኛ ለም ሆቴል አካባቢ ለሚኩራ ሰሚት አቦ ማዞሪያ ብስራተ ገብኤል አንበሳ ጋራጅ ገርጂ መብራት ሀይል አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ፓርኮችን ለማከራየት
  • ሎት 2 : ኮልፌ ፓርክ አቃቂ ፓርክ ከንቲባ ቢትወደድ፣ አምባሳደር እና ሸገር ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሱቆች ካፍቴሪያ አዳራሾች ለጂም ቤት የሚሆኑ ቤቶችን ለማከራየት
  • ሎት 3 በፈረንሳይ ፓርክን የችግኝ ጣቢያውን ሳይጨምር ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡
  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት ፡፡
  2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና የተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል።
  3. የሚሰጠውን አገልግሎት የሚገልጽ አጭር እና ግልጽ ፕሮፖዛል ማቅረብ አለበት፡፡
  4. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና መናፈሻዎችን የመጸዳጃ ቤቶችን የጽዳት የጥበቃ፣ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑ ማስጠገን መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል።
  5. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
  6. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የስራ ሰአት ቅዳሜ እና እሁድ በአላትን እንዲሁም ምሽትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል፡፡
  7. አሸናፊነት ከታወቀ በኋላና ውል ከወሰደ በኋላ 3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል፡፡
  8. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሊደር ልማቱን የሚመጥን አጋዎችን ይዞ መግባት የሚችል፡፡
  9. ከተቻለ በሬስቶራንት በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል
  10. ተጫራቾች ለሎት አንድ እና ሁለት 50,000.00 (ሀምሳ ብር) ሎት 3 100,000.00 (አንድ መቶ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 230 እስከ 130 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ ባለው 11ኛው ቀን ጠዋት 400 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  13. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400-ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 430 ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
  14. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 0703614456 /0977246014 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን

 

Save Tender