የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በአዲስ አበባ ውስጥ ለንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን እና 4ኪሎ ፖስታ ቤት 4ኛ ፎቅ ለመከራየት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ማስታወቂያ
የሚከራዩ የንግድ ቤቶች የጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግጨ22/17
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በአዲስ አበባ ውስጥ ለንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን እና 4ኪሎ ፖስታ ቤት 4ኛ ፎቅ ለመከራየት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈልና የሚከራዩ ቤቶችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 2ኛ ፎቅ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
ቤቶቹን የሚከራዩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ድረስ ሰነዱ ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾ በቅድሚያ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው።
የጨረታው ሰነድ የሚመለስበት ቀን ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ ብቻ ነው፡፡
በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስል ቁጥር 09 11 95 45 37 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት
