በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አግሮ ክላስተር ስር የሚተዳደረው ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር በስሩ ከሚያስተዳድራቸው እርሻዎች መካከል አንዱ በሆነው እና ከአዲስ አበባ 435 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው ጎጀብ እርሻ የሚገኙ የተለያዩ ቁመት እና ስፋት ያላቸው ባህር ዛፎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
MIDROC ENVESTMENT GROUP
የባህር ዛፍ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር HP/0006/17
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አግሮ ክላስተር ስር የሚተዳደረው ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር በስሩ ከሚያስተዳድራቸው እርሻዎች መካከል አንዱ በሆነው እና ከአዲስ አበባ 435 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው ጎጀብ እርሻ የሚገኙ የተለያዩ ቁመት እና ስፋት ያላቸው ባህር ዛፎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን በሟማላት መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ሰነዱ ጋር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 8፡30 ድረስ ዘውትር በስራ ቀናት እና ሰዓት ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመቅረብ መግዛትና የጨረታ መልስ መስጠት አለባቸው።
- ጨረታው ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ መልስ መስጫ ሰነድ ሲመለስ ማንኛውም ለውጥም ሆነ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. /CPO/ ብቻ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911064781/0911899634 አዲስ አበባ እና 0917100154 ጎጅብ እርሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን አለፍ ቢሎ በሚገኘው ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ጎን ነው::
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
