አጋር ሁለገብ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
አጋር ሁለገብ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ማሰራት ይፈልጋል
ሎት 1. በማህበሩ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የተለያዩ አገልግሎት የሚሆን የግንባታ እና የሻተር ስራ
ሎት 2. የመዝናኛ ተቋም ክበብ የአንድ ዓመት የአዲት ስራ
ሎት 3. ለመዝናኛ ክበብ የሚሆን የባንኮኒ እና የካሸር መቀመጫ
ሎት 4. በማህበሩ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ፍርስራሽ ቆርቆሮዎችና የተለያዩ ብረቶችን ሽያጭ መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ የጋበዝን መሆናችንን እየገለፅን ለመወዳደር ማሟላት ያለባችሁ መስፈርቶች-
- በየዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የሚጫረትበትን 2% ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ / በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ
- ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት የሚችል እና የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በሚያቀርበው የውል ሰነድ ህጋዊ የውል ስምምነት መዋዋስ የሚችል
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን የማህበሩ ፅ/ቤት በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-2-73-96-71 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፦ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 18 ማዞሪያ ይምቦርሽ ሆቴል አጠገብ፡፡
አጋር ሁለገብ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት
ስራ ማህበር
