በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለትምህርት ጽ/ቤት ለተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ህትመት እና ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለትምህርት ጽ/ቤት ለተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ህትመት እና ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡- ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለመጻሕፍቱ እና ስለፈርኒቸሩ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሎተ 1 ተጫራቾች ለመጻሕፍት ህትመት ለጨረታው ማስከበሪያው /CPO/ 20,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ፣
ሎት 2 ተጫራቾች ለፈርኒቸር ግዢ ለጨረታው ማስከበሪያው /CPO/ 15,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
- የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተባለው ሰዓት ታሽጎ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ ሆኖም ለአንድ እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 21 33 86 96 /09 33 62 02 20
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ፋ/ጽ/ቤት
