የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከኢስት አፍሪካ ናሽናል ዲስትሪቢዩሽን አ.ማ (ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ) ወደ ተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማድረስ ፈልጎ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ክፍል አንድ
የጨረታ ቁጥር አመሥድ 20/2017
የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከኢስት አፍሪካ ናሽናል ዲስትሪቢዩሽን አ.ማ (ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ) ወደ ተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማድረስ ፈልጎ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሲሚንቶው የሚጫንበት ቦታ |
መለኪያ |
የሚጫነው ሲሚንቶ ብዛት |
ሲሚንቶው የሚራገፍበት ቦታ |
ምርመራ |
|
1 |
ኢስት አፍሪካ ናሽናል ዲስትሪቢዮሽን አ.ማ (ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ) |
ኩ/ል |
4500 |
ደሴ |
|
|
7500 |
ወራቤ ቦጆበር |
|
|||
|
12000 |
ባ/ዳር |
|
|||
|
3000 |
ወልዲያ |
|
|||
|
3000 |
ደምበጫ ፈረስ ቤት |
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ.እ. ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፍኬት ቁጥር (TIN) እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- አስር (10) እና በላይ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ያሉት እና የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ወይም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲ.ፒ. ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ የባንክ ጋራንቲ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የጭነቱን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ማለትም የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የተሽከርካሪዎችን ሊብሬ ኮፒ እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማስገባት ዋና እና ቅጅ ለብቻ፣ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያን ለብቻ በፖስታ በማሸግ ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ እና አቅርቦት ቡድን በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ኮርፖሬሽናችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
