የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ በ2017 በጀት አመት ንብረትነቱ የዋግ ልማት ማህበር የሆነው ማርያም አካባቢ የሚገኘውን ዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ ጨረታ አውጥቶ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
የአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋልማ/ ጨ-1/ /2017
የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ በ2017 በጀት አመት ንብረትነቱ የዋግ ልማት ማህበር የሆነው ማርያም አካባቢ የሚገኘውን ዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ ጨረታ አውጥቶ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘርፋ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የ2017 ዓ.ም የታደሠ ፈቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN ያላቸው)፣
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተወዳዳሪዎች በስማቸው የተመዘገበ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲ መኪና ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግ/ፋ/አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የሚገዙበት የማይመለስ ብር በ200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጋዜጣው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር---2-- በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው በወጣ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 2 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስልክ ቁጥር፡- 0335400837 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/
