ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - Service 0004/2017
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 003 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በዚሁ መሠረት ፡-
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን ሽሮሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ከግንቦት 04 ቀን 2017 ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።
- በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራች 50,000.00 (ሃምሣ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፣
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ 3ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፣
ሲፒኦውን በማንኛውም ባንክ በሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ስም ማሰራት ይችላሉ።
ዋጋ ሲያስቀምጡ ስርዝ ድልዝ ወይም በተመለከተው ሠንጠረዥ መሠረት በትክክልና በግልጽ የዋጋ ማቅረቢያ መሠረት ግልጽ መረጃ መስጠት ያለበት ሲሆን ነገር ግን አሻሚ የሆነ ሰነድ ቢገኝ ውድቅ ይሆናል፡፡
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር
