የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በIFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን (Audit firm) አወዳድሮ በማስመርመር ማዘጋት ይፈልጋል፡፡
የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- APF/23/2017/LOCAL
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በIFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን (Audit firm) አወዳድሮ በማስመርመር ማዘጋት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለ2017 በጀት ዓመት በሙያው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከAccounting and Auditing Board of Ethiopia ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት (TN Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ (VAT) ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 2 ላይ የተገለፀው ቢኖርም የጨረታ ሠነዱን መግዣ ዋጋ በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በኢ-ሜይል አድራሻችን amharapipefactory@gmail.com በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ በኢ-ሜይል በማግኘት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ጨምሮ “Amhara Pipe Factory” የጠቅላላ የአገልግሎት ዋጋውን 2% ከባንክ በፋብሪካችን ስም በተዘጋጀ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተ.ቁ 1 ላይ የተገለፁትን የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና ሌሎች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሠነዶችን በአንድ ላይ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው ክዋጋ ማቅረቢያው (Financial Bid Offer) በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እንዲሁም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን (Financial Bid Offer) እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው ከላይ በተ.ቁ 5 ላይ ከተገለፁት ከቴክኒክ መስፈርት በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 በፋብሪካው ግቢ ውስጥ በዕለቱ የሚከፈተው የቴክኒክ የመጫረቻ ሠነድ ብቻ ይከፈታል፡፡
- 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ፋብሪካው ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡-09 35 98 37 29/ 09 18 70 18 26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግ/ኩባንያ
